ሩሲያ በ2024 በአውሮፓ ሕብረት ሁለተኛዋ ትልቅ ጋዝ ላኪ ሆነች

ሩሲያ በ2024 በአውሮፓ ሕብረት ሁለተኛዋ ትልቅ ጋዝ ላኪ ሆነች ሩሲያ በ2024 ወደ አውሮፓ ሕብረት የምትልከውን ጋዝ ወደ 54.45 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በማሳደግ፤ አሜሪካን መቅደም እንደቻለች ስፕትኒክ በብሩጌል መረጃ ላይ ያካሄደው ትንታኔ ያሳያል። በ2024 የአውሮፓ ሕብረት 297.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ጋዝ የገዛ ሲሆን፤ ሕብረቱ ከሩሲያ የሚገዛው ጋዝ ድርሻ ከ2023 ጋር ሲነፃፀር በ21% ጨምሯል። በአጠቃላይ የሩሲያ የአውሮፓ ሕብረት የጋዝ ገበያ ድርሻ ከ14.2% ወደ 18.3% ከፍ ብሏል። ባለፈው ዓመት ወደ አውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ጋዝ የላካቸው ኖርዌይ ብቻ ነች- ከ2023 90.3 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ጋር ሲነፃፀር 93.3 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ነው። በ2023 ለአውሮፓ ሕብረት ሁለተኛዋ ከፍተኛ ላኪ የነበረችው ዩናይትድ ስቴትስ፤ በ2024 አቅርቦቷን በ18% ቀንሶ፤ 51.3 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በመላክ ሶስተኛ ደረጃ ይዛለች። በዚህም ድርሻዋ በዓመት ውስጥ ከ19.7% ወደ 17.2% ቀንሷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik