ከኒጀር ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ናይጄሪያ ከኒያሚ ጋር የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ ለማከናወን ቁርጠኛ እንደሆነች የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ የናይጄሪያ የደህንነት ባለስልጣናት፤ የኒጀር ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱራሃማኔ ቲቺያኒ፤ ናይጄሪያ ፈረንሳይ ቀጣናውን ለማተራመስ የምታደረገውን ጥረት ትደግፋለች እንዲሁም በቦርኖ ግዛት የጦር ሰፈር እንድታቋቁም ገንዘብ ተቀብላለች በማለት ያቀረቡትን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል። የናይጄሪያ መንግሥት በጉዳዩ ዙርያ ባወጣው መግለጫ፤ በቀጣናው ያለውን ሽብርተኝነትን ለማጥፋት ቁርጠኛ እንደሆነ በማረጋገጥ፤ ክሱን “መሰረተ ቢስ” ሲል ውድቅ አድርጓል። የመከላከያ ሚዲያ ኦፕሬሽን ዳይሬክተሩ ሜጀር ጄኔራል ኤድዋርድ ቡባ፤ ውጥረቱ ቢኖርም ናይጄሪያ ከኒጀር ጦር ኃይሎች ጋር የጋራ ዘመቻዎችን ለመቀጠል እንደምትሻ ተናግረዋል። የኒጀር መንግሥት የናይጄሪያ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚን ጠርቶ፤ ናይጄሪያ በውጭ ኃይሎች እና በቀድሞ የኒጀር መንግሥት ባለስልጣናት ተባባሪነት፤ ግዛቷን ለማተራመስ ዓላማዎች እያዋለች ነው ሲል ከሷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia