የሱዳኑ መሪ አል-ቡርሃን ከአማፂው አርኤስኤፍ ጋር ከጦርነት በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስን ውድቅ አደረጉ የሱዳን 69ኛ የነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በቴሌቭዥን ቀርበው ንግግር ያደረጉት የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን፤ ወደ ቀደመው ሁኔታ መመለስ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ፤ አማፂውን ፈጥን ደራሽ ኃይል (RSF) "ነፍሰ ገዳይ እና ወንጀለኛ" ብለውታል። "ከሚያዝያ 15 ቀን 2023 በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስ ወይም እነዚህ ነፍሰ ገዳዮች፣ ወንጀለኞች እና ደጋፊዎቻቸው በሱዳን ህዝብ መካከል እንዲኖሩ አንፈቅድም" ሲሉ አል-ቡርሃን ተናግረዋል። ግጭቱን ለማስቆም እና የተፈናቀሉ ሰላማዊ ዜጎች በሰላም ወደነበሩበት የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ለታለሙ እውነተኛ የሰላም ጅምሮች ክፍት መሆናቸውን የገለጹት መሪው፤ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በሱዳን ውስጥ መቆየት እንደማይቀሉ በማያሻማ መልኩ ገልጸዋል። ግጭቱ በሚያዝያ 2023 ከተቀሰቀሰ ጀምሮ፤ ወደ 25,000 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን እና ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት መፈናቀላቸውን በመጥቀስ፤ ጦርነቱ ያስከተለውን አስከፊ ኪሳራም አንስተዋል። ጦርነቱ በሀገሪቱ ከፍተኛ ውድመት በማድረስ ሚሊዮኖችን ወደ ረሃብ እና ሞት አፋፍ የገፋ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ የሽምግልና ጥረቶች እስካሁን ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ማምጣት አልቻሉም።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia