ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የፋይናንስ ዘርፉን ማጠናከር ላይ ያነጣጠረ የ700 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራርሙ

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የፋይናንስ ዘርፉን ማጠናከር ላይ ያነጣጠረ የ700 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራርሙ የብድር ስምምነቱ ለፋይናንስ ዘርፍ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት የሚውል ነው። ፕሮጀክቱ ቁልፍ የሚባሉ የፋይናንስ ዘርፍ ማሻሻያዎች እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፤ የካፒታልና የፋይናንስ መዋቅሮችን ለማረጋጋት የሚያደረጉትን ጥረቶች ለመደገፍ ስትራቴጂካዊ በሆነ ሁኔታ መዘጋጀቱ ተገልጿል። ገንዘቡ መንግሥት በቅርቡ የባንኩን ዘርፍ ለማዘመንና የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የፈቀደበትን ማሻሻያ እንደሚደግፍ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። አብዛኛው የስምምነቱ ፋይናንስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል መዋቅር የማስተካከያ ሥራዎች ላይ እንደሚውል ተመላክቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik