ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት ወደ ውጭ ከላከችው ወርቅ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ አገኘች

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት ወደ ውጭ ከላከችው ወርቅ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ አገኘች ገቢው በቅርቡ የተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ያስገኘው ውጤት ነው ሲል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ባለፈው የበጀት ዓመት ሀገሪቱ ወደ ውጭ ከላከችው የወርቅ ምርት 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማግኘቷን የገለጹት ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ፤ ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ከወርቅ የወጪ ንግድ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል። በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ለወርቅ የወጪ ንግድ፣ የእንስሳትና ሌሎች ዘርፎች ስኬት ወሳኝ ሚና መጫወቱን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik