ሴኔጋል በ2025 ከውጪ ሀገራት ወታደራዊ ተጽእኖ ለመላቀቅ እንዳሰበች የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ይፋ አደረጉ "በመከላከያ እና ደህንነት መስክ አዲስ የትብብር መርህ እንዲያቀርቡ ለጦር ኃይሎች ሚኒስትሩ መመሪያ ሰጥቻለሁ። ይህም ከ2025 ጀምሮ በሴኔጋል ውስጥ ያለ ማንኛውም የውጭ ወታደራዊ ኃይል እንዲወጣ ያደርጋል" ብለዋል ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ። ንግግራቸው የግዜ ገደብ ሳይሰጡ የፈረንሳይ ጦር በሀገሪቱ የነበረው ቆይታ እንደሚያበቃ ማስታወቃቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። ፈረንሳይ በጋቦን፣ ሴኔጋል እና ኮትዲቯር ያሏትን ወታደሮች ወደ 100 ለመቀነስና የድጋፍ ሚና ብቻ እንዲጫወቱ ማቀዷን የፈረንሳይ ሚዲያ ባለፈው ዓመት መጀመሪያ ዘግበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia