ቤኒን አሸባሪዎችን ትደግፋለች በሚል የቀረበባትን ክስ ለመቃወም በሀገሪቱ የኒጀር ጉዳይ አስፈጻሚን ጠራች የቤኒን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “በመሰረተ ቢስ ውንጀላ” ለኒጀር ጉዳይ ፈጻሚ ጥሪ ቢያቀርብም፤ ሀገሪቱ ለውይይት እና ለወንድማማቻዊ ትብብር ቁርጠኛ እንደሆነች ገልጿል። የቤኒን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሉሴጉን አድጃዲ ባካሪ፤ ለኒጄር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፃፉት ደብዳቤ፤ የኒጀር መሪ አብዱራሃማኔ ቲቺያኒን ንግግር እንደተቃወሙና ከወዲሁ የሀገሪቱን ልዑክ ተቀብለው እንዳነጋገሩ የዲፕሎማሲ ምንጮችን ያጣቀሱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ቲቺያኒ ፈረንሳይ እና ቤኒን ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ ሲሉ የከሰሱ ሲሆን፤ ቤኒን ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ለሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ቡድኖች ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ታቀርባለችም ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia