በተጓዦች መብት ጥሰት ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጄሪያ አቪዬሽን ባለሥልጣን ደንቦችን ለማክበር ቃል ገባ" እነሱ [ኢትዮጵያ አየር መንገድ] በቀጣይ የናይጄሪያን ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ደንቦችን ለማክበር ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል እናም እስከ እሁድ [ዛሬ] ድረስ ሪፖርት እንደሚልኩ ተናግረዋል" ሲሉ የናይጄሪያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በዚህ ሳምንት በተከሰቱት የበረራ መስተጓጎሎች ላይ የተሳፋሪዎች ቅሬታዎች እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ማዕቀብ ከተጣለባቸው አየር መንገዶች ተወካዮች ጋር ከቅዳሜ ከተደረገው ስብሰባ በኋላ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። የናይጄሪያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን፤ ተመላሽ ገንዘብ አዘግይተዋል፣ ተገቢ ያልሆነ ሻንጣ አያያዝ አላቸው እንዲሁም ከባለስልጣኑ መመሪያዎች አላከበሩም ያላቸውን አምስት አየር መንገዶች ማዕቀብ ጥሎባቸዋል ሲሉ የናይጄሪያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የህዝብ ጉዳዮች እና የደንበኞች ጥበቃ ዳይሬክተር የሆኑት ማይክል አቺሙጉ በዚህ ሳምንት በአቡጃ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።ማዕቀቡ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን ተጠያቂነት ለማሻሻል ያለመ መሆኑን አቺሙጉ ጠቁመው፤ አየር መንገዶቹ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና ከፍተኛ የበዓል ወቅት እንኳን ቢሆን በወቅቱ ገንዘብ የመመለስ እና ተገቢ የመንገደኞች ጓዝ አያያዝ ኃላፊነት እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።" እንደ ሃርማታን [ይህ ከምዕራብ ሰሃራ የሚነፍስ ነፋስ ሲሆን በመኸር መጨረሻና በክረምት ወቅት በጣም ኃይለኛ ይሆናል] ያሉ ያልተጠበቁ ኩነቶች በአየር መንገዶቹ ጥፋት ውስጥ አልተካተቱም። ይሁን እንጂ እነዚህ ማዕቀቦች አየር መንገዶቹ ለተጓዦች ያላቸውን ግዴታ ባለመወጣታቸው የተጣሉ ናቸው" ብለዋል።ከሁለት ሳምንታት በፊት ማይክል አቺሙጉ፤ በናይጄሪያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ደንብ 2023 መሠረት ለተጓዞች ተመላሽ ገንዘብን የሚያዘገዩ ማንኛውም አየር መንገዶች ላይ ማዕቀብ እንደሚጣል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል ሲል ባለስልጣኑ ዛሬ እሁድ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia