እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡ ወታደሮቿን ካርታ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም በማለት የሀማስ ባለስልጣን ተናገሩ ሀማስ ባለፈዉ ረብዑ ፤ በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ወታደሮችን ስለማስወጣት ፣ የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ እና የእስረኛ ልውውጥ አስመልክቶ እስራኤል "አዲስ ሁኔታዎችን" አስቀምጣለች በማለት ተናግረዋል። " በአሁኑ ጊዜ ጠላታችን (እስራኤል) ወታደሮቿ ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡበትን ግልፅ የሆነ ካርታ ለመሰጠት ፍቃደኛ አይደለችም ፤ በየት እና እንዴት እንደሚወጡ ማሳወቅ አትፈልግም። ጦርነቱን ለማቆም ግልፅ እና የመጨረሻ ቃላትን ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም" በማለት የሀማስ የፖሎቲካ ቢሮ አባላት የሆኑት ባስም ናም ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ናም ጨምረውም ባለቤትነታቸው ፍልስጤም ቡድኖች የሆኑ የጦር መሳሪያዎች ጉዳይ በተኩስ አቁሙም ሆነ በጋዛ ሰርጥ እስረኛ ልውውጥ ድርድር ወቅት ያለመነሳቱን ጠቅሰዋል። " የኛ አቋም በሁለቱም ድርድሮች እና በሌሎችም ፣ የፍልስጤም ህዝቦች ናቸው እነርሱ በሀይል ተይዘዉ እስካሉ ድረስ ፤ ራሳቸውን ከሀይል አገዛዝ ነፃ የመውጣት እና የራሳቸውን ሀገር እስኪመሰርቱ ድረስ ፤ በሀይል መያዛቸውን በማንኛውም ህጋዊ ሁኔታ የመቃወም መብት አላቸው ይሄ ታጥቆ ማመፅንም ያካትታል" በማለት ተናግሯል። በእገታው ላይ የመጀመሪያው ድርድር ከተደረገ ከአንድ አመት በኋላ እስራኤል እና ሀማስ ድርድራቸውን በአሸማጋዩች አማካኝነት የቀጠሉ ሲሆን ስለቀሪ ታጋቾች እየተደራደሩ ይገኛሉ። በቅርቡ በካይሮ እና በዶሃ ውጥረቶች የበዛባቸው ንግግሮች እየተካሄዱ ሲሆን የታየ መሻሻል አለመኖሩን ምንጮች ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia