የአዝአል አውሮፕላን በሩሲያ የአየር ክልል ውስጥ ሳለ ለውጭ ተፅዕኖዎች ተጋልጦ ነበር በማለት የአዜርባጃን ፕሬዝዳንት ተናገሩ የአዜርባጃን አየርመንገድ አውሮፕላን ምስጋና ለፕሮፌሽናል አብራሪዎቹ እና መሬት ተጋጭቶ ሊያርፍ ችሏል በማለት የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት የፕሬስ አገልግሎት ሃላፊ ኢልሃም አሊዬቭ በዛሬው እለት ተናግረዋል። ግጭቱን ለመመርመር የአለምአቀፍ ባለሙያዎች ኮሚሽን መቋቋሙን አሊዬቭ አስረድተዋል። የባልስቲክ እና ተቀጣጣይ ነገሮች ባለሙያዎች ምርመራ እንዲያካሂዱ መመደባቸውን ፤ የካዛክስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ካናት ቦዙምባዬቭ ጠቅሰዋል። ከአዘርባጃን መዲና ባኩ ወደ ሩሲያዋ ቼቼን ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ግሮዝንይ እየበረረ የነበረው አውሮፕላን ታህሳስ 16 ጠዋት በምዕራብ ካዛኪስታን አኩቱአ ከተማ አቅራቢያ መውደቁ ይታወሳል። አየርመንገዱ 62 ተሳፋሪዎችን እና አምስት የበረራ አስተናጋጆች ይዞ ነበር። የካዛክስታን የአደጋ ጊዜ ሚኒስቴር እንደገለፀዉ ከአደጋው 29 ሰዎች ተርፈዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia