የናይጄሪያ መከላከያ አዛዥ የውጭ ሀገር ወታደራዊ ሰፈሮችን ውድቅ አደረጉ፤ የገናን በዓል ከወታደሮች ጋር አከበሩ፤ ለብሔራዊ ደህንነት ያላቸውን ቁርጠኝነትም በድጋሚ አረጋግጠዋል

የናይጄሪያ መከላከያ አዛዥ የውጭ ሀገር ወታደራዊ ሰፈሮችን ውድቅ አደረጉ፤ የገናን በዓል ከወታደሮች ጋር አከበሩ፤ ለብሔራዊ ደህንነት ያላቸውን ቁርጠኝነትም በድጋሚ አረጋግጠዋልየናይጄሪያ የመከላከያ ሠራዊት አዛዥ ጄኔራል ክሪስቶፈር ግዋቢን ሙሳ የገናን በዓል ከፋንሳን ያማ (ከሃውሳ ቋንቋ የተገኘ እና "ከምእራብ ሀጥያት ነፃ መውጣት" የሚል ትርጓሜ ያለው) ኦፕሬሽን ወታደሮች እና ከሶኮቶ ግዛት ከፊት መስመር ወታደሮች ጋር እንዳከበሩ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።ጄኔራል ሙሳ የናይጄሪያ ጦር ኃይሎች የሀገሪቱን ግዛታዊ አንድነት ለመከላከል ያላቸውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል። በናይጄሪያ የውጭ ወታደራዊ ሰፈሮች ማቋቋምን በጥብቅ በመቃወም ወታደሩ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ስጋቶችን የመቋቋም አቅም እንዳለው አፅንዖት ሰጥቷል። “በጎረቤት ሀገሮቻችን ላይ እንደ ለሚፈጸም ጥቃት የናይጄሪያ አንድ ኢንች መሬት እንኳን ማስጀመሪያ መድረክ ሆኖ እንዲያገለግል ለማንም አንፈቅድም” ሲሉ መገለጻቸው ተገልጿል።የናይጄሪያ የመከላከያ ሠራዊት ወንጀለኞችን ለሚያስጠልሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆን ለጸጥታ ያልተባበሩ ተደርገው እንደሚቆጠሩ ገልጿል። ትብብርን በማበረታታት ዜጎች በጋራ ጠላቶቻቸው ላይ አንድ ሆነው እንዲቆሙ እና የወንጀል አካላትን ከመደገፍ እንዲቆጠቡ አሳስቧል። "ወንጀለኞችን የሚያስጠልል ማንኛውም አካል የፀጥታ ችግር ላይ በሚደረገው ትግል ውስጥ ዒላማ ሊሆን ይችላሊ" ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።ለፕሬዚዳንት ቲኑቡ፣ ለሶኮቶ ግዛት አመራር እና ለወታደሮቹ ምስጋናቸውን የገለጹት ጄኔራል ሙሳ፣ ወታደሮቹ የከፈሉትን መስዋእትነት በማድነቅ፣ ስንሰርዓት እና ትኩረታቸው ይዘው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik