የኮሮና ቫይረስ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ ለተከሰተው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ መነሻ ሆኖ እንደተለየ ተዘገበ የኮንጎ ብሄራዊ ባዩሚዲካል ምርምር ኢኒስቲትዩት በሰጠው ማጠቃለያ ቀደም ብሎ ተከስቶ የነበረው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ውስብስብ የሆነ የኮንፌክሽን (አንድ ሴል ብዛት ባላቸው ቫይረሶች ሲጠቃ የሚፈጠር) ነው ብሏል ሲል የኮንጎው የዜና ማሰራጫ አክቱአሌት ዘግቧል። በኮንጎ የተለዪት የበሽታ ፓቶጅኖች ከኢንፉሌንዛ ቫይረስ AH1N1 እና ከኮሮና ቫይረስ SARS -CoV -2 ተመሳሳይነት አላቸው። እነዚህ ፓቶጅኖች ከወባ በሽታ ጋርም ግንኙነት አላቸው ። ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ሰውነት በተዳከመበት ወቅት ነው። በጎርጎሮሳዊያኑ ታህሳስ 17 አለምአቀፍ የሳይንቲስቶች ቡድን ይህ ያልታወቀ በሽታ የከፋ የወባ ነው ብለው ነበር ። ይሁንእንጂ የቀጠለው ምርምር በሽታው የተወሰኑ ቡድኖች ፓቶጅን እንዳለው አሳይቷል።ይህ በኮንጎ ክዋንጎ ባለፈው ጥቅምት የተከሰተው በሽታ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት እና የከፋ የራስ ህመም ያስከትላል ። ከኮንጎ መንግስት እንደተገኘው ይፋዊ መረጃ አሁን ላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 593 ሲሆን 36 ሞት ተመዝግቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia