ብሪክስ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን መሰረት ያደረገ የሎጅስቲክስ ማእከል ሊገነባ ነው፤ ለምን አስፈላጊ ሆነ? የብሪክስ ቢዝነስ ምክርቤት ዩኤኢን መሰረት ያደረገ የሎጅስቲክ ማእከል ስለመፍጠር እየተወያየ መሆኑን የምክርቤቱ የሩሲያ ቅርንጫፍ ሊቀመንበር የሆኑት ሴርጌ ካትይሪን ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል።የሎጅስቲክ ማእከሉ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳው በካዛን በነበረው የብሪክስ ጉባኤ ወቅት ነበር ፤ በመቀጠልም ትብብርን የማሳደግ አስፈላጊነት በተከታታይ መግለጫዎች ላይ ተንፀባርቆ ነበር። በኢንዲያና ፣ ፓስፊክ እና አትላቲክ ውቅያኖስ መሀከል ቁልፍ የሆኑ የንግድ መስመሮች የሚገናኙባት የዩኤኢ እስትራቴጂካዊ አቀማመጥ እንዲሁም ወደቦቿን ፣ አየር ማረፊያዎቿን እና የተቀናጀ የመንገድ ኔትወርኮቿን የሚያካትተው መሰረተ ልማቶቿ ለሎጅስቲክስ ማእከሉ ተመራጭ አድርጓታል።ብዛት ያላቸው አስፈላጊ የትራንስፖርት ኮሪደሮች በብሪክስ አባላት መሀከል ያለውን ግንኙነት እና የጋራ ንግድ ያጠናክረዋል፦▪አለምአቀፉ የሰሜን- ደቡብ ትራንስፖርት ኮሪደር (INSTC) 7200 ኪሎሜትሮችን የሚሸፍን ሲሆን ሩሲያን ፣ ኢራንን ፣ ህንድን ፣ ቻይናን እና ካዛክህስታንን ያገናኛል።▪የምስራቅ -ምእራብ የትራንስፖርት ኮሪደር 10,000 ኪሎሜትሮችን አካባቢ የሚሸፍን ሲሆን ቻይናን ፣ ሩሲያን ፣ ካዛክህስታንን ፣ አዘርባጃንን ፣ አርመኒያን ፣ እና ቱርክ ከአውሮፓ የሚያገናኝ እና ከቻይና "ዋን ቤልት ዋን ሮድ" ፕሮጀክት ጋር አብሮ የሚሄድ ነው።እንደ የአለም ንግድ ድርጅት የቅርብ መረጃ በብሪክስ አባል ሀገራት መሀከል እንዲሁም በአለምአቀፍ አጋሮቻቸው መሀከል ያለው የንግድ ግንኙነት በጎርጎሮሳዊያኑ 2023 መጨረሻ 10.4 ትሪሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር። ይህም ቁጥር የአለምን 21.6 በመቶ ንግድ መጠን ይወክላል።የሩሲያ የንግድ በጎርጎሮሳዊያኑ 2024 የመጀመሪያ አምስት ወራት በ2023 ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 6.3 በመቶ አድጓል ያሉት የሩሲያ ኢንዱስትሪ እና ንግድ ሚኒስትር የሆኑት አንቶን አሊክሃኖቭ ባለፈው ነሀሴ ባቀረቡት ሪፖርተር ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia