እስራኤል በየመን ላይ የምታደርገውን የአየር ጥቃት "አሁን ነው የጀመረችው" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ተናገሩ

እስራኤል በየመን ላይ የምታደርገውን የአየር ጥቃት "አሁን ነው የጀመረችው" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ተናገሩ " ከእነርሱ ጋር ጋር ገና መጀመራችን ነው ... አሁን ላይ እስራኤልን እንዳያጠቁ አንፈቅድላቸውም ዛሬም ሆነ ሌላ ቀን። በመራር ሁኔታ እስኪማሩ ድረስ እንደበድባቸዋለን። እንዳልኩት ሀማስ ተምሯል ፣ ሄዝቦላ ተምሯል ሶርያም ተምራለች። ሀውቲዎችም የሚማሩ ይሆናል " ብለዋል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁን በመጥቀስ የእስራኤል ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል። የእስራኤል ተዋጊ ጀቶች ባደረሱት ስድስትና የአየር ጥቃቶች በየመን ዋና ከተማ ሰንአ በ የመን ሙቭመንት አንሳር አላህ ወይም ሀውቲ ተብሎ በሚጠራው የታጣቂዎች ስብስብ ቁጥጥር ስር የሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ እንደወደመ ምንጮች በትላንትናው እለት ለስፑትኒክ ተናግረዋል። በትላንትናው እለት ቆይቶ የእስራኤል መከላከያ ሀይሎች በሰነአ ላይ በደረሰው ጥቃት የአለም የጤና ድርጅትን ልኡካንን ከያዘው አውሮፕላን አቅራቢያ የሚገኝ ህንፃ መውደሙን አረጋግጠዋል። የሟቾች ቁጥር ስድስት ሲደርስ 40 ሰዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል። በባለፈው ሳምንት ሀውቲዎች እስራኤል ለምታደርሰው ጥቃት ተገቢ የሆነ ምላሽ እንደሚሰጡ አስፈራርተዋል። የሀውቲ ጦር ቃል አቀባይ ያየህ ሳሬ እንዳሉት እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ በጋዛ ሰርጥ እየፈፀመች ያለችው ወንጀል "ለበለጠ ጥቃቶች" ሊያመራ እንደሚችል እና ከኢራቁ የ ኢስላሚክ ሪሲስታንስ ቡድን ጋር የጋራ ተልእኮ ሊኖራቸው አንደሚችል ተናግረዋል። ከማህበራዊ ትስስር ገፆች የተገኙ ምስሎች የእስራኤል ጥቃት በሰነአ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና ሁዳኢዳ ወደብ ያደረሰውን ውደመት የሚያሳዩ ናቸው ተብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik