የአፍሪካ ህብረት በሞዛምቢክ የተከሰተው የርስ በርስ አለመረጋጋት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ"የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት መንግስት እና ሁሉም የፖለቲካ እና ማህበራዊ ተዋናዮች ተጨማሪ የህይወት መጥፋትን እና የንብረት ውድመትን ለማስወገድ ቀውሱን በሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈቱ አሳስበዋል" ሲል ድርጅቱ ሐሙስ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።ማሃማት አክለውም የፀጥታ ኃይሎች የኃይል አጠቃቀማቸ በመቆጠብ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም በተከሰተው ሁከቱ ምክንያት የሚወዷቸውን ሰዎች ላጡ ሰዎች ጥልቅ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።ሊቀመንበሩ ህብረቱ የዓመፅ ድርጊቱን ለማስቆም እና የሀገሪቱን ዴሞክራሲ ለመጠበቅ ከሞዛምቢክ ባለሥልጣናት ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል። ሰኞ ዕለት የሞዛምቢክ ህገ መንግስታዊ ምክር ቤት በጥቅምት ወር የተካሄደውን የምርጫ ውጤት አረጋግጧል። ይህን ተከትሎም በመላ አገሪቱ አመጽ ተነስቷል።በሞዛምቢክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት መገለጹን ተከትሎ በሞዛምቢክ ዋና ከተማ በተነሳው ተቃውሞ ቢያንስ 50 ሰዎች በጥይት መቁሰላቸውን የሞዛምቢክ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዕለት ዘግበዋል። ብሉምበርግ የዜና ወኪል እንደዘገበው በጎርጎርሳውያኑ ጥቅምት 9 ከተካሄደው ምርጫ በኋላ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ በአጠቃላይ186 ሰዎች ሞተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia