የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፌሌክስ ሺሴኬዲ የሀገሪቱን ሕገ-መንግሥት ለማሻሻል ዝግጁ መሆናቸውን በድጋሚ አረጋገጡ "እናንተን ለማገልገል ዝግጁ ነን። ሕገ-መንግሥቱ እንዲቀየር የምትሹ ከሆነ እንቀይረዋለን። ባለበት እንዲቆይ ከፈለጋችሁ፣ ባለበት እናስቀጥለዋለን” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ታህሳስ 15 ቀን ለካናንጋ ህዝብ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ገልጸዋል። ዜጎች በሂደቱ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የጠየቁት ሺሰኬዲ፤ በሕገ-መንግሥቱ ማሻሻያ ላይ የመጨረሻው ውሳኔ በቀጥታ በሉዓላዊው ሕዝብ ላይ እንደሚያርፍ ተናግረዋል። "ሕገ-መንግሥታችን ጥሩ አይደለም። በባዕድ ሀገር ሰዎች የተጻፈ ነው። የእኛን እውነት መሰረት ያደረገ ሕገ-መንግሥት ያስፈልገናል" ሲሉም አክለዋል። የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያ ሕገ-መንግሥት በፈረንጆቹ 1964 ከነጻነት አራት ዓመት በኋላ፤ ሁለተኛው ደግሞ በ1967 ሥራ ላይ ውሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia