የባማኮ ጎዳናዎች የማሊን ታሪክ በሚዘክሩ ስያሜዎች ተቀየሩ "ይህ እርምጃ ታሪካችንን ለማደስ እና ጀግኖቻችንን እና ጀግኒቶቻችንን ለማክበር ያለንን ጽኑ እና ቆራጥ ፍላጎት ያሳያል" ብለዋል የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላዬ ማዪጋ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታህሳስ 15 ቀን ከዚህ በፊት የኢኮዋስ አደባባይ ተብሎ የሚጠራው አደባባይ፤ የኤኢኤስ አደባባይ በሚል ስያሜ በተቀየረበት ኦፊሴላዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው እንደነበር፤ ጽሕፈት ቤታቸው ያወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል። ማዪጋ አክለውም የቦታዎቹ ስያሜ ለውጥ ሀገራዊ እሴቶችንና ማንነትን ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል። በባማኮ ዙርያ ወደ ሠላሳ የሚጠጉ መንገዶች፣ አደባባዮች እና የሕዝብ ተቋማት “ብሔራዊ፣ አፍሪካዊ፣ ፓን-አፍሪካዊ እና ዓለም አቀፋዊ ስብዕናዎችን እና እውቅ ግለሰቦችን ለመዘከር” በድጋሚ መሰየማቸውን ጋዜጣዊ መግለጫው ጨምሮ ገልጿል። በሀገሪቱ ሌሎች አካባቢዎችም ስያሜዎችን የመቀየር እቅድ ተይዟል። በሌላ በኩል፤ “እንደ ዴ ላ አርቶይስ አደባባይ፣ ዴ ላ ማርኔ ወይም ሩ አርኪናርድ አደባባይ ያሉ ስያሜዎች በማሊያውያን የጋራ ትውስታ ውስጥ ምንም ዓይነት ስሜት አይሰጡም” ብሏል ጋዜጣዊ መግለጫው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia