ግብፅ በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ተልዕኮ ውስጥ እንደምትሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታወቁ ግብፅ የወቅቱን የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) በሚተካው በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) የሚኖራት ተሳትፎ፤ በሶማሊያ መንግሥት ጥያቄ መሠረት እንደመጣ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ከሶማሊያ አቻቸው አህመድ ሙአሊም ፊቂ ጋር ካይሮ ውስጥ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ መስማማታቸውን አስታውቀዋል። ግብፅ እና ሶማሊያ በነሐሴ ወር አጋማሽ የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። የግብፅ ወታደሮች እና መሳሪያዎች ወደ ሀገሪቱ መግባታቸውን፤ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በህዳር ወር መገባደጃ ዘግበዋል። የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ካይሮ የሶማሊያ ደህንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አትፈቅድም ሲሉ ቀደም ብለው ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia