የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የደኅንነት ተቋማት በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ጸረ-ሰላም ኃይሎችን ለመግታት የጋራ ግብረ-ኃይል ለማቋቁም ለመሥራት ተስማሙ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የጅቡቲ ሪፐብሊክ የሴኪዩሪቲ ዶክመንቴሽን ሰርቪስ፤ በሁለቱ ሀገራት ድንበሮች አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ጸረ-ሰላም ኃይሎችን በመግታት ዙርያ ምክክር አካሂደዋል። ሁለቱ ሀገራት ከመረጃ ልውውጥ ባሻገር፤ የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁመው ስምሪት ለማከናወንና ወንጀለኞችንም አሳልፎ ለመስጠት መስማማታቸውን፤ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የሁለቱን ሀገራት የጋራ ስጋቶች መመከት የሚያስችሉ እንዲሁም ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማምጣት የሚረዱ ጉዳዮች ዋንኛ የምክክሩ አጀንዳዎች እንደነበሩ ተጠቁሟል። ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ በኩል የምታከናውነው የወጪ ገቢ ንግድ ላይ የሚስተዋሉ የደኅንነት ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ውይይት መካሄዱንም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመልክቷል፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia