የትራምፕ የዩክሬንን ግጭት የማስቆም ፍላጎት በስልጣን ሽኩቻ የተገፋፋ እንጂ ከሩሲያ ጋር የቅርብ ግኑኝነት በመኖሩ አይደለም ሲሉ የቀድሞው የዩክሬን ፖለቲከኛ ተናገሩ "ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም እንደሚፈልጉ አሁን ግልጽ ሆኗል። ዲፕ ስቴትን በመዋጋት ላይ ማተኮር ይፈልጋሉ፣ የአሸማጋይ እውቅና ምናልባትም የኖቤል የሰላም ሽልማት ማግኘት ይፈልጋሉ" ሲሉ የቀድሞው የዩክሬን ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ኦሌግ ዛሬቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ኤለን መስክ ለዩክሬን ወታደራዊ መሳሪያዎች ለመስጠት በአሜሪካ ኮንግረስ የፀደቀውን ሕግ፤ የተሳሳተ ነው ማለቱ እንደሚያስማማቸው ዛሬቭ ገልጸዋል። የትራምፕ አሸናፊነት ግልፅ ሲሆን፤ ጆ ባይደን አሸንፋለሁ ብለው በሚጠብቁት ወቅት ከነበረው አቋማቸው ጋር በሚጋጭ መልኩ፤ ጦርነቱን ለማራዘም መስራት መጀመራቸውንም ጠቁመዋል። "[ዶናልድ ትራምፕ] የዩክሬን ጦርነትን መቆም የሚደግፉ እጩዎችን ሾመዋል። ይህ ትክክል፣ ጥሩ እና የምንቀበለው ነው። ሆኖም ትክክለኛውን ምክንያት ልንረዳ ይገባል። ቭላድሚር ፑቲንን ወይም ሩሲያን ስለሚወዱ አይደለም። የስልጣን ሽኩቻ ስላለ ነው" ሲሉ አክለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia