'በምእራባውያን ያለመፈለግ ስሜት' የደቡብ ግሎባል ሀገሮች ከብሪክስ ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዲያድግ አድርጓል በማለት ፕሮፌሰሩ ተናገሩ በዩስአይዩ - አፍሪካ ውስጥ የታሪክ እና አለምአቀፍ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ማቻሪያ ሙኔኔ ፤ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጎርጎሮሳዊያኑ አመት መጨረሻ በሚደረገው አመታዊ የቀጥታ ጥያቄና መልስ እንዲሁም ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ብሪክስ ምእራባዊያንን መቃረኛ አይደለም ብለው ግልፅ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። " ጂ -ሰባትንም ሆነ ሌሎችን የምእራባውያንን ቡድኖች መቃረን አስፈላጊ አይደለም ። ይሄ ብዙ ሀገሮችን የሚያገናኝ የራሱ የሆነ እሴት ያለው ስብስብ ነው ወደፊትም እንደዚሁ ነው በግልፅ እየቀጠለ የሚሄደው " በማለት ፕሮፌሰሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ማችሪያ ሙኔኔ እንዳመኑት " በጣም ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች በብሪክስ ቡድን እየተሳቡ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ የምእራቡ አለም የበላይነት አማራጭ እየሆነ በመምጣቱ ነው" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia