የታህሳስ 11 ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦ ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሱዳንን ውስጣዊ ውይይት እንዲደግፍ እና ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም ምክር ቤቱ በሱዳንን ጉዳይ ባደረገው ስብሰባ ላይ መጠየቋን በመንግስታቱ ድርጅት የሩሲያ ቋሚ ተወካይ ቫሲሊ ኔቤንዝያ ገልጹ። የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ የጦር ኃይሎችን ዋና አዛዥና ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናትን በሌሎች ኃላፊዎች ተክተዋል። ይህም ባለፉት አመታት ከተደረጉት ትልልቅ ለውጦች መካከል አንዱ መሆኑን የሀገሪቱ የመንግስት ቴሌቪዥን ሐሙስ ዕለት ዘግቧል። በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የታየው የጉንፋን መሰል በሽታ በረሃብ በተዳከመ ህዝብ ላይ የሚከሰት በአካባቢው የተለመዱ በሽታዎች ውህድ ሊሆን እንደሚችል አፍሪካ ሲዲሲ ገልጿል። በሞስኮ በደረሰው የሽብር ጥቃት በጀኔራል ኪሪሎቭና ረዳታቸው ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ ሩሲያ የደረሰው በመኸር ወቅት እንደነበር ህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች አስታዉቀዋል። የሩሲያ አየር መከላከያ ኃይል በትላንትናው ምሽት 36 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አቅጣጫ ማስቀየሩን እና ማውደሙን የመከላከያ ሚኒስቴር አሳወቀ። የአውሮፓ ህብረት 130 ቢሊዩን ዩሮ ለዩክሬን ማውጣቱን የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ለይን አስታወቁ። ኒውዮርክ በሚገኘው የእስራኤል ቆንስላ ላይ ሊደርስ የነበረውን የሽብር ድርጊት እንደተከላከሉት የቆንሱላው ጀነራል ኦፊር አኩኒስ ተናገሩ። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ማክሮን በአውሎንፋስ በተመታው የማዮቴ ኦቨርሲስ ዲፓርትመንት ንግግር እንዳያደርጉ ተደረገ። ይህ ተፈጥሯዊ አደጋ 30 ሞት እና ከ800 ሚሊዩን ዩሮ ውድመት አስከትሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia