ያልተቋረጠው የእስራኤል መንደር መስፋፋት በክልሉ ያለውን ውጥረት በይበልጥ እያቀጣጠለው ነው ፤ በማለት የተመድ ባለስልጣን ተናገሩ " በዌስት ባንክ ያለው እና ምስራቅ እየሩሳሌምን ያካተተው የእስራኤል መንድር መስፋፋት እጅግ አሳሳቢ በሆነ መልኩ ያለማቋረጥ እየቀጠለ ነው ፤ ይህም በአካባቢው ያለውን ውጥረት በይበልጥ በማቀጣጠል ላይ ይገኛል። በአካባቢው የሚኖሩ ፍልስጤማውያን መሬታቸውን በመከልከል ወደፊት የምትፈጠረዋ ራስዋን የቻለች ፣ ዲሞክራሲያዊት ፣የራስዋ ድንበር ያላት ሉአላዊነት ፍልስጤም እንዳትኖር እንቅፋት ይፈጥራል" በማለት የመካከለኛው ምስራቅ ፣ ኢሲያ እና ፓስፊክ የተመድ ፀሀፊ ጀነራል ምክትል የሆኑት ሞሀመድ ካህሊድ ካሂሪ ተናግረዋል። የተመድ ባለስልጣኑ አክለውም በእስራኤል በተያዘው የዌስት ባንክ ፣ ምስራቅ እየሩሳሌም ጨምሮ ሌሎች ሰፈራዎች በሙሉ በተመድ አቋም መሰረት "ህጋዊ መሰረት የሌላቸው" እንደሆኑ አስታውሰዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia