የታህሳስ 9 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦

የታህሳስ 9 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፈረንሳይ እና ቤልጂየም የሚገኙ የአፕል ተቀጥላ ድርጅቶች በአቅርቦት ሰንሰለታቸው የግጭት ማዕድኖችን ተጠቅመዋል በማለት ክስ እንዳቀረበች የከሳሽ ጠበቆች ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። አፕል በበኩሉ አቅራቢዎች ያልተሞከሩ ቁሳቁሶችን መግዛት እንዲያቆሙ መጠየቁን ገልጿል። 🟠 የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) በ2027 ኢኮ ነጠላ ምንዛሪን ለማስተዋወቅ ዝግጅቱን እንደቀጠለ ተገለጸ። 🟠 ኬንያ አብዛኛውን የሀገሪቱ ክፍል ያዳረሰ ከፍተኛ የመብራት መቆራረጥ በትናንትናው እለት ገጠማት። የኃይል አቅርቦቱ ከስድስት ሰዓት በኋላ ተመልሷል ሲል የኬንያ ኃይል ኩባንያ ገልጿል። 🟠 የሩሲያ ራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ኢጎር ኪሪሎቭ ገዳይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሩሲያ ፌደራል ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ። 🟠 አራት የዩክሬን ድሮኖች በቤልጎሮድ፣ ብራያንስክ እና ኩርስክ ክልሎች ሌሊቱን ተመተው መውደቃቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ። 🟠 የአሜሪካ ኢሌክቶራል ኮሌጅ የመጨረሻውን ውጤት እና የዶናልድ ትራምፕን አሸናፊነት አረጋገጠ። ትራምፕ 312 ድምጽ፤ ካማላ ሃሪስ ደግሞ 226 ድምጽ አግኝተዋል። 🟠 ተሰናባቹ የባይደን አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ የጸደቀውን ቀሪ 5.6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ወደ ዩክሬን ለመላክ ጊዜ እንደማይኖረው የፔንታጎን ከፍተኛ ባለስልጣን ለኒውዮርክ ታይምስ ተናግረዋል። 🟠 የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ከአመፅ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለፖሊስ ጥያቄ ሳይገኙ እንደቀሩ ዮንሃፕ የዜና ወኪል ዘግቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik