የዶንባስ ግስጋሴ፦ ማክሲሚሊያኖቭካን የተቆጣጠሩት የሩሲያ ሀይሎች ኩራኮቮ ላይ ትኩረታቸውን አድርገዋል የጠላት ዋና የመድፍ ይዞታ የሆነው ማክሲሚሊያኖቭካ ከከፍተኛ መከላከል በኋላ መያዙን ተከትሎ፤ በኩራኮቮ አካባቢ ለሚደረገው ጥቃት መንገድ ጠርጓል ብሏል አንድ የሩሲያ ወታደር። "እጅ የሚሰጡ ከሆነ በጥይት እንደሚመታቸው አዛዣቸው ጮሆ ሲናገር ሰምተናል። እስከ መጨረሻው ወታደር ድረስ ተቋቁመዋል" ሲል 6 ፀረ-ታንክ ፈንጂዎች ስትራቴጂካዊ ቦታውን ለመያዝ ጥቅም ላይ እንደዋሉ ጠቁሟል። ወታደሩ ከተያዙት የጦር እስረኞች ስለ ጠላት እንቅስቃሴ ወሳኝ መረጃ መገኘቱንም ጠቅሷል። "አሁን በከበባ "በመዳፋችን" ውስጥ ለመክተት እየተንቀሳቀስን ነው። ከተማውን ለመቆጣጠር ብዙ ግዜ እንደማይወስድብን አስባለሁ፤ ነገር ግን መዘናጋት የለብንም። በየቀኑ እየሰራን እና ወደ ፊት እየገፋን ነው" ሲል ወታደሩ ተናግሯል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia