ናይጄሪያዊው አዴሞላ ሉክማን የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ

ናይጄሪያዊው አዴሞላ ሉክማን የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ የአትላንታው (ጣሊያን) አማካይ ሰኞ እለት በሞሮኮ ማራኬሽ በተካሄደው ሁነት ሽልማቱ እንደተበረከተለት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታውቋል። ሉክማን ተፎካክሮ የነበረው ከሲሞን አዲግራ (ብራይተን እና ሆቭ አልቢዮን፤ ኮትዲቯር)፣ ሰርሁ ጉይራሲ (ቦሩሺያ ዶርትሙንድ፤ ጊኒ)፣ አሽራፍ ሃኪሚ (ፒኤስጂ፤ ሞሮኮ) እና ሮንዌን ዊሊያምስ (ማሜሎዲ ሰንዳውንስ፤ ደቡብ አፍሪካ) ጋር ነበር። የ27 ዓመቱ ሉክማን አትላንታ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ባነሳበት የፍፃሜ ጨዋታ ሃትሪክ በመስራት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የአፍሪካ ዋንጫን ያሸነፉት የኮትዲቯር አሰልጣኝ ኤመርሴ ፋ ምርጥ አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል። ምስሎቹ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የተገኙ ናቸው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik