ቺዶ ዓውሎ ነፋስ በማዮት እና ኮሞሮስ ውድመት ካደረሰ በኋላ ሞዛምቢክን መቷል በካቦ ዴልጋዶ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ፔምባ አቅራቢያ ከባድ ዝናብ እና በሰዓት 200 ኪሎሜትር የተመዘገበ ኃይለኛ ንፋስ ደርሷል። ሆኖም ወደ መሀል ሀገር ሲገፋ ኃይሉ እንደቀነሰ ተነግሯል። በህንፃዎች ላይ ጉዳት መድረሱን እና አንዳንድ አካባቢዎች መብራት ማጣታቸውን ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በካቦ ዴልጋዶ ግዛት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስት ኩባንያ ዘግቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia