ሩሲያ ሥራቸውን ሲሠሩ ሕይወታቸውን ያጡ ጋዜጠኞችን በዛሬው እለት አስባ ውላለች

ሩሲያ ሥራቸውን ሲሠሩ ሕይወታቸውን ያጡ ጋዜጠኞችን በዛሬው እለት አስባ ውላለች በዩክሬን ግንባር የተገደሉት የሚዲያ ባለሙያዎች ዝርዝር መጨመሩን ቀጥሏል ሲሉ፤ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ቀኑን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል። ዛካሮቫ የኪየቭ መንግሥት ሆን ብሎ ጋዜጠኞች ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ዘመቻ እንደጀመረ እና በምዕራባውያን መንግሥታት እና የዓለም አቀፍ የደህንነት ድርጅቶች እውቅና ለዓመታት የቀጠለ ነው ሲሉም ከሰዋል። ዩኔስኮ በቅርቡ በጋዜጠኝች ደህንነት ላይ ያወጣው ሪፖርት የሩሲያን ጋዜጠኞች ሞት ችላ ብሏል በማለትም ትችት ሰንዝረዋል። በዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ አማካኝነት የቀረበው ሪፖርት የሩሲያ ልዑካን እና የደቡባዊ ዓለም አጋራት ባደረጉት ጥረት ይሁንታ ሳያገኝ ቀርቷል። ዛካሮቫ አክለውም ምዕራባውያኑ ለአዞላይ የሚሰጡት ድጋፍ የጋዜጠኞች ደህንነትን በተመለከተ አቋም እንደሌላቸው የሚያጋልጥ ነው ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik