በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የሩዋንዳ መሪዎች መኻከል በአንጎላ ሊካሄድ የታቀደው የሰላም ድርድር ተሰረዘ

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የሩዋንዳ መሪዎች መኻከል በአንጎላ ሊካሄድ የታቀደው የሰላም ድርድር ተሰረዘ የሩዋንዳ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መሪዎች በአንጎላ ፕሬዝዳንት ጃዎ ሎሬንሶ አደራዳሪነት እሁድ ሊያካሂዱት የነበረው ድርድር፤ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ሳቢያ እንደተቋረጠ፤ የአንጎላ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። እንደ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ገለጻ ከሆነ፤ ሩዋንዳ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኤም23 አማፂ ቡድን መኻከል ቀጥተኛ ውይይት እንዲደረግ በመጠየቋ ምክንያት ድርድር ሊቆም ችሏል። የኤም23 ህልውና በሩዋንዳ ወታደራዊ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው የሚለው የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት፤ ቀጥተኛ የድርድር ሃሳቡን እንደማይቀበል ገልጿል። የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪየር ንዱሁንጊሬህ በቡኩላቸው፤ ኪጋሊ "ግልጽ በሆነ ማዕቀፍ እና የግዜ ሰሌዳ ከኤም23 ጋር ቀጥተኛ ድርድር ለመቀጠል ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጽኑ አቋም" እንደምትፈልግ አርብ እለት ተናግረዋል። የአንጎላ ሽምግልና በነሀሴ ወር የተኩስ አቁም አሳክቶ የጦር ግንባሩን ለጊዜው ቢያረጋጋም፤ ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ ውጊያው ተባብሷል። በማዕድን የበለፀገው ምሥራቃዊ ኮንጎ በርካታ ታጣቂ ቡድኖችን ባሳተፈ ውስጣዊ እና ድንበር ተሻጋሪ ግጭቶች፤ ለአስርት ዓመታት ሲታመስ ቆይቷል። የመሪዎች ጉባኤው ቢሰረዝም፤ ሁለቱ ሀገራት በአንጎላ የሚመራ የተኩስ አቁም ጥሰት ተቆጣጣሪ የጋራ ኮሚቴ በቅርቡ አቋቁመዋል። የሩዋንዳ ወታደሮች ከኮንጎ ግዛት የሚወጡበትን መንገድ የተመለከተ ሰነድም በሁለቱ ሀገራት ጸድቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik