የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሀገሪቱ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ42 ሚሊየን በላይ ማድረሱ ተገለጸ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማስፋትና ከሀገራዊ ማሻሻያ ጋር በማጣጣም ከፍተኛ ለውጥ ያመጣውን የ2025ቱን ስትራቴጂ ስኬት ለማስቀጠል፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መቅረጿን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮ ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል መዞሩ እና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ፤ በሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎትን በከፍተኛ ደረጃ በማስፋት ተጠቃሚዎችን ከ17 ሚሊዮን ወደ 42.5 ሚሊዮን በላይ እንዳሳደገ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎትን እንዳሻሻለ ሚኒስቴሩ ገልጿል። በተጨማሪም መንግሥት ከ800 በላይ የኦንላይን አገልግሎቶችን እንዳስጀመረና የኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂን ተግባራዊ በማድረግ እና ተጨማሪ የዲጂታል መንግሥት ውጥኖችን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የ "5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች" መንግሥታዊ መርሃ ግብርም በዲጂታል የሰለጠነ የሰው ኃይል መገንባት ላይ እንዳነጣጠረ ተገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia