ኒጀር የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን የሚኒስትሮች ስብሰባን አስተናገደች

ኒጀር የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን የሚኒስትሮች ስብሰባን አስተናገደች ስብሰባው በማሊ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱላዬ ዲዮፕ ሊቀመንበርነት፤ የሌሎች አባል ሀገራት ተወካዮች በተሳተፉበት ታህሳስ 4 ቀን ተካሂዷል። ሚኒስትሮቹ ህዳር 13 ባማኮ ውስጥ ተካሂዶ የነበረውን የስብሰባ ውጤት አጽድቀዋል። ስብሰባው የደህንነት ጉዳዮችን እንዲሁም መታወቂያና ፓስፖርቶችን በኮንፌዴሬሽኑ ውስጥ አንድ ማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ መክረዋል። በቅርቡ ወደ ትግበራ እንደሚገባም የመጨረሻው መግለጫ አመልክቷል። አባል ሀገራቱ ከኢኮዋስ አባልነት ለመውጣት ያደረጉትን የማይሻር ውሳኔ ሚኒስትሮቹ በድጋሚ አረጋግጠዋል። የተለያዩ ኮሚቴዎች የህዝቡን ጥቅም በማስቀደም፤ በአወጣጡ ተግባራዊ ጉዳዮች ዙርያ ውይይታቸውን እንዲቀጥሉም አሳስበዋል። ሐምሌ ወር 2024 በኒያሚ የጉምሩክ አስተዳደር የፀደቀው በሀገራቱ የጉምሩክ ስርዓት ውህደት ፕሮጀክት ውስጥ ቶጎን የማካተት ሂደትም ተረጋግጧል። የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን በአብሮነት እና በትብብር ለዜጎች የተሻለ መጪ ግዜን ለመፍጠር ቁርጠኛ እንደሆነ በድጋሚ አረጋግጧል። ይህም የኢኮኖሚ ውህደት፣ የተሻለ ደህንነት እና ህዝብን የሚያገለግል አስተዳደር ላይ ትኩረት ማድረግን ይጨምራል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik