በማሊ በተደረገ ፀረ- ፈረንሳይ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰልፈኞቹ የፕሬዝዳንት ማክሮንን ቅርፅ አቃጠሉበትላንትናው እለት በማሊ ባማኮ የተሰበሰቡት እና በቁጥር 150 የሚደርሱት ሰልፈኞች የፈረንሳይ መንግስት በቅኝ ግዛት ዘመን ላደረጋቸው ድርጊቶች ካሳ ጠይቀዋል። የሰልፉ አስተባባሪዎች ፈረንሳይ በማሊ ዜጎች ላይ ለፈፀመችውን ወንጀል በተጨማሪ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ1960-2020 ፈፅማለች ባሉት አሻጥር በጥልቀት ክስ አቅርበዉባታል። ሰልፉ የፈረንሣዩን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቅርፅ በማቃጠል ተጠናቋል። በጎርጎሮሳውያን ህዳር 18 የተጀመረው እና በትላንትናው ሰልፍ ላይ የተነሳውን የካሳ ሀሳብ የሚደግፈው የበየነመረብ ፊርማ ማሰባሰብ ሂደት 100,000 ፊርማዎችን ማሰባሰብ ችሏል። የፋይናንስ ኤክስፐርት የሆነው አማዱ አልፋ ሲሶኮ ነበር ይህንን የካሳ ጥያቄ እንዲጀመር ያነሳሳው። በሱ ግምገማ መሰረት ፈረንሳይ ከሳህል አካባቢ ሀገራት ጋር ትክክለኛ ትብብር እንዲኖራት ለማድረግ ቅድሚያ በቅኝ ግዛት ግዜ ለፈፀመችው ብዝበዛ ተገቢውን ካሳ መክፈል ይኖርባታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia