አፍሪካ ቅኝ ግዛትን እና አፓርታይድን እንድትዋጋ የረዳቻት ሞስኮ ማስታወስ አለባት የደቡብ አፍሪካው እስፖርት ጥበብ እና ባህል ሚኒስቴር" ተዋጊዎቻችን በሞስኮ ነበር የሰለጠኑት ፤ ለነፃነት ትግላችን አበርክቶት ነበራቸው ። ሩሲያን ሳንጠቅስ ስለ ትግላችን ማውራት አንችልም " በማለት ጋይቶን ማሲኬንዚ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል። የአፍሪካን ሀገሮች የነፃነት ትግል እንቅስቃሴዎች ትዝታ ማቆየት አስፈላጊ ነው ያሉት ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ለሚያከናውኗቸው ተግባራት ደቡብ አፍሪካ እና አንጎላ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት ነው። "አሁንም ድረስ በአንጎላ ውስጥ የተቀበሩ ጀግኖች አሉን በአንጎላ መንግስት እርዳታ ወደ ቤታቸው የምናመጣቸው ይሆናል። ይሄ የአሁኑ ስምምነት አንዱ አካል ነው" በማለት ሚኒስተሩ ተናግረዋል።በጎርጎሮሳዊያኑ 1975 ነበር አንጎላ ከፖርቹጋል ቅኝ ገዢነት ራሷን ነፃ ማውጣቷን ያወጀችው። የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ መንግስትም በጎርጎሮሳዊያኑ 1994 ወድቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia