በሶሪያ ያለው ሁኔታ በሰሜን ሊባኖስ የሚገኙ ኢስላማዊ ቡድኖች እንዲነሳሱ እያደረገ መሆኑን ምንጮች አጋለጡ

በሶሪያ ያለው ሁኔታ በሰሜን ሊባኖስ የሚገኙ ኢስላማዊ ቡድኖች እንዲነሳሱ እያደረገ መሆኑን ምንጮች አጋለጡ "የሶርያው ቀውስ ከጀመረበት ከጎርጎሮሳውያኑ 2011 ጀምሮ በአካባቢው የነበሩት ፅንፈኛ ሀይሎች አሁን ላይ እንቅስቃሴአቸውን ማጠናከር ጀምረዋል። ለረጅም ግዜ በሊባኖስ በመቆየታቸው ድንበር መሻገር አላስፈለጋቸውም" በማለት በትሪፖሊ የሚገኝ የሊባኖስ ፖለቲካ ምንጭ ለስፑትኒክ ተናግሯል። በሰሜን ሊባኖስ የሚገኙ የአክራሪ ቡድን መሪዎች ከሶሪያ ተቃዋሚ ታጣቂዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው በማለት ምንጩ ጨምሮ ገልጿል። "የአክራሪነት አመለካከት ካላቸው ቡድኖች ለህዳጣን ተወካዩች ደህንነት የሚጠቅም ነገር ያመጣል ብሎ መጠበቅ የሚያዋጣ አይደለም ፤ ይህም የሀይማኖት ነፃነትን ይጨምራል። ከትእዛዛቸው አንዷን ማጉደል አደገኛ ነው ፤ ይህም በመሀከላቸው አለመግባባትን ፈጥሯል ሁኔታውም አሳሳቢ ነው" በማለት ምንጩ ተናግሯል። የሰሜን ሊባኖስ የቀድሞ አልዊቴ ህግአውጭ የነበረዉ አሊ ዳርዊሽ ለስፑትኒክ እንደተናገረው በሶሪያ ያለው የኃይል ለውጥ በሰሜን ሊባኖስ የሚገኙ ለውጡ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መሀከል ክፍፍልን ፈጥሯል። ይሁን እንጂ የጦሩ እና የፀጥታው አገልግሎት የተፈጠሩትን ሁኔታዎች በቁጥጥር ስር አውለውታል በማለት ዳርዊሽ አክለው ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik