የታህሳስ 3 ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦ የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ ለኢኮዋስ መሪዎች የቡርኪና ፋሶ፣ የማሊ እና የኒጀር ዜጎች ጥቅም እና ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኖ እንደሚቀጥል ገለጹ። ዲፕሎማሲ እና ጥበብ ሀገሮቹን በቀጠናዊው ድርጅት ውስጥ ለማስተሳሰር መሪ መርሆዎች እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል። በተያዘው ጎርጎሮሳውያኑ ዓመት በመጀመሪያዎቹ 10 ወራት ሩሲያ ከ21 ሚሊዮን ቶን በላይ ስንዴ ወደ አፍሪካ ሀገራት መላኳንና ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ35 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን ፣ የአግሮኤክስፖርት ማዕከል ገልጿል። የሩሲያ አየር መከላከያ ኃይሎች ባንድ ምሽት 16 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በሩሲያ ክልሎች ማውደማቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታዉቋል። የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፊኮ አውሮፓ ከሩሲያ ጋር መደበኛ ውይይት መጀመር አለባት ሲሉ ተናግረዋል። ዶናልድ ትራምፕ የቻይናውን ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በጎርጎሮሳውያኑ ጥር 20 ቀን 2025 በአሜሪካ መዲና በሚካሄደው በዓለ ሲመታቸው ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ለተጠረጠሩበት አመጽ በማስነሳት ወንጀል ክስ ሂደቶች ዝግጁ መሆናቸውን መግለጻቸውን ዮንሃፕ የዜና ወኪል ዘግቧል የሃማስ ንቅናቄ ግጭቱ ካበቃ በኋላ የእስራኤል ኃይሎች በጋዛ ውስጥ ለጊዜው እንዲቆዩ የሚያስችል ስምምነት ላይ ሊስማማ እንደሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ ማስታወቁን ሪፖርቶች ገለፁ ለበርካታ ሳምንታት በኒው ጀርሲ የአሜሪካ ግዛት ላይ ያልታወቁ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ሲበሩ ሰንብተዋል። የአካባቢው ባለሥልጣናት ምርመራ እንዲካሄድ ቢጠይቁም ፔንታጎን ግን ምንም ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia