ሩሲያና-አፍሪካ በትምህርት ፣ በግብርና እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ይበልጥ እንዲተባበሩ የሩሲያ ሰብአዊ እርዳታ ካውንስል ጥሪ አቀረበ

ሩሲያና-አፍሪካ በትምህርት ፣ በግብርና እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ይበልጥ እንዲተባበሩ የሩሲያ ሰብአዊ እርዳታ ካውንስል ጥሪ አቀረበ " ከ4800 በላይ አፍሪካውያን ተማሪዎች የሩሲያ መንግስት ብቻ ባመቻቸው የስኮላርሺፕ እድል ተጠቅመው ለትምህርት ወደ ሩሲያ ይጓዛሉ" በማለት የተናገሩት የሩሲያ መንግስት የሲቪል የውጭ እርዳታ እና ባህል ልውውጥ የሮሶትሩድኒቼስትቮ ሃላፊ የሆኑት ይቭገኝ ፕሪማኮቭ "በፈጠራ የተሞላ ተግባር : ሳይንስ ሲደመር ቢዝነስ" በሚል ርእስ በሞስኮ እየተደረገ ባለው ኮንግረንስ ላይ ነው። ወሳኝ ቁጥር ያላቸው የህክምና ተማሪዎች በሩሲያ በትምህርት ላይ ናቸው ፤ ነገርግን በምግብ ዋስትና እና ግብርና ዘርፍ ላይ ያሉ ተማሪዎች ቁጥር አሁንም ዝቀተኛ መሆኑን ፕሪማኮቭ አስረድተዋል ።" እኛ ሩሲያውያን በእርግጠኝነት ለእድገት የሚሆን ክፍት ቦታ አለን ምክንያቱም የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ላይ የምንሰራው ስራ ምግብ በማቅረብ ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም" በማለት ሀላፊው አፅንኦት በመስጠት ተናግሯል። የሩሲያ-አፍሪካ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ላይ ያላቸው ትብብር ምግብ በማቅረብ ብቻ ሳይሆን ሎጀስቲክሱንም በማገዝ ነው ፤ ይህም የምግብ ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ ፣ በግብርና ዘርፍ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ላይ ስልጠና በመስጠት እንዲሁም የፋይናንስ ዘርፉ እና ከላይ ከተዘረዘሩት ነጥቦች ጋር እርስ በእርሱ የተያያዘ መሆኑን ባለስልጣኑ ተናግረዋል። አሁን ላይ አፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ላይ የገጠማትን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሩሲያን እርዳታ በተለይም በቴክኖሎጂ ዘርፍ የማግኘት ፍላጎት አላት ፤ ሮሶትሩድኒቼስትቮም ይህንን የማስፈፀም ብቃት እና ስልጣን አለው በማለት የቢሮው ሀላፊ ተናግረዋል። ተናጋሪው መጪዎቹ ፕሮጀክቶች አፍሪካን መሰረት ያደረጉ መሆን እንዳለባቸው እና በግብርናው ዘርፍ ያሉ የአፍሪካ እና የሩሲያ ድርጅቶች ተግባር ተኮር ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውበታል ፤ ይህ ተግባራዊ በሆነ መልኩ የሚደረግ የአጋርነት ሂደት ለአፍሪካ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶች መፍትሄ ይሆናል ብለዋል።" ከዚህ ቀደም የተደረጉ ተግባራዊ የሆኑ ፕሮጀክቶች ወይ በሶቺ ወይም በሞስኮ በአጠቃላይ በሩሲያ ምድር ላይ ነበር ፤ ነገርግን ይህ የሩሲያ-አፍሪካ ፎረም ሌጋሲ ወደ አፍሪካ ምድርም መተላለፍ አለበት። የአፍሪካን ችግር ከአፍሪካ ውጭ መፍታት የማይታሰብ ነው" በማለት ኤጀንሲያቸው በጎርጎሮሳዊያኑ ሚያዝያ 2025 ይህንን ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነ ሀላፊው ጨምረው ጠቁመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik