የቻድ መንግሥት ለፕሬዝዳንት ዴቢ ኢትኖ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ሰጠየቻድ የሽግግር ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት፤ ለፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ የሀገሪቱን ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ፊልድ ማርሻል ለመስጠት የተላለፈውን ውሳኔ፤ በ160 ደጋፍ፣ በ6 ድምፀ ተአቅቦ እና በ2 ተቃውሞ ማጽደቃቸውን፤ የሽግግር ብሔራዊ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በመንግሥት ባለስልጣናት እና ቁጥራቸው ቀላል በማይባሉ የምክር ቤት አባላት የተደገፈው የውሳኔ ሃሳብ፤ የዴቢ ኢትኖን ጀግንነት፣ ታማኝነት እና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ያሳዩትን ቁርጠኝነት ጠቅሷል ሲል መግለጫው አመልክቷል። አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ማዕረጉ የተሰጠበት ግዜ ላይ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፤ አብላጫዎቹ የፕሬዝዳንቱን ተግባር በማድነቅ የክብር ማዕረጉን ተገቢነት እንደተቀበሉ መግለጫው ጨምሮ ገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia