ሶሪያ የጸጥታው ምክር ቤት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊ የእስራኤልን ጥቃት እንዲያስቆሙ ጥሪ አቀረበች "በሶሪያ መንግሥት አቅጣጫ መሰረት ለዋና ፀሀፊውና ለፀጥታው ምክር ቤት የእስራኤልን ጥቃት የሚያወግዝ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የፀጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነትን የማስጠበቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡና እስራኤል በሶሪያ ላይ የምታደርሰውን ጥቃት እንድታቆም የሚጠይቁ ተመሳሳይ ደብዳቤዎችን አስተላልፈናል" ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት የሶሪያ አምባሳደር ኩሳይ አል-ዳህክ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የሶሪያው ዲፕሎማት አክለውም፤ እስራኤል በአሁኑ ወቅት ሶሪያ ውስጥ የተፈጠረውን ሽግግር ለወረራ አጀንዳዋ እንዳትጠቀምበት፣ ዓለም አቀፍ ህግጋትን፣ የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን እና የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን እንድታከብር ጠይቀዋል። እስራኤል በሶሪያ ግዛት ላታኪያ ወደብ የሶሪያ ባህር ሃይል ላይ ሰኞ እለት በተከታታይ ጥቃት እንዳደረሰች ተዘግቧል። ምስሎቹ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የተገኙ ናቸውበእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia