ማሌዢያ የብሪክስ አጋር ሀገር እንድትሆን የቀረበላትን ጥያቄ በይፋ እንደተቀበለች የሀገሪቱ መልዕክተኛ ተናገሩ በሩሲያ የማሌዢያ አምባሳደር ቼንግ ሉን ላይ፤ ማሌዢያ በህዳር ወር አጋማሽ ይፋዊ ጥያቄ እንደቀረበላት እና ለወቅቱ የብሪክስ ሊቀመንበር ሩሲያ አዎንታዊ ምላሽ እንደሰጠች ለሩሲያ ሚዲያ አረጋግጠዋል። በቅርቡ በካዛን ከተማ በተካሄደው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በርካታ ሀገራት የብሪክስ አጋር እንዲሆኑ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል። ፑቲን የሃገራቱን ሙሉ ዝርዝር ይፋ ከማድረግ ግን ተቆጥበዋል። ፑቲን፤ በቀጣይ ተጨማሪ ግብዣዎች እንደሚላኩ እና የአጋር ሀገራት የመጨረሻ ዝርዝር አወንታዊ ምላሽ ከተሰጠው በኋላ ይፋ እንደሚሆን አብራርተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia