መስከረም 29 በተካሄደው የሞዛምቢክ ምርጫ ዙርያ ቅዳሜ እለት በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በትንሹ 20 ሰዎች ሲቆስሉ በማፑቶ ሁለት የመንግሥት ህንጻዎች በእሳት ጋዩየተቃዋሚ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ቬናንሢዮ ሞንድሌን፤ አዲስ የተቃውሞ ምዕራፍ በመጪው ረቡዕ እንደሚጀምርና ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ አስታውቀዋል። የብሔራዊ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኦርላንዶ ሙዱማኔ እንዳሉት፤ በማፑቶ ተቃዋሚዎች መንገዶችን ለመዝጋትና የመንግሥት ህንጻዎችን ለማጥቃት የተቃጠሉ ጎማዎችን እና የቤት ውስጥ ቦንቦችን ተጠቅመዋል። በአስለቃሽ ጭስ ምላሽ ከሰጡት ፖሊሶች ጋር በተፈጠረ ግጭት 20 የሚደርሱ ሰዎች ቆስለዋል። "የፖሊስ ክፍሎችን ከማጥቃታቸው እና መሳሪያዎቻቸውን ከመንጠቃቸው በፊት መበተን ችለናል" ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል። ሞንድሌን፤ የገዥው ፓርቲ ፍሬሊሞ የምርጫ ድልን በመቃወማቸው በተቀሰቀሰው የድህረ ምርጫ ብጥብጥ፤ እስካሁን በትንሹ 90 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን 340 የሚሆኑት ቆስለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia