የሶሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር በሀገሪቱ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መጀመሩንና ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት መፍጠራቸውን ገለጹ በሶሪያ ስላለው ሁኔታ እስካሁን የታወቁ ነገሮች፦🟠 የሶሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ጋዚ ጃላሊ የሩሲያ ጦር በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ቆይታ በተመለከተ አዲሱ መንግሥት እንደሚወስን ገልጸዋል። 🟠 ባለስልጣኑ ፕሬዝዳንት አሳድ የት እንዳሉ እንደማያውቁ፣ ለመጨረሻ ጊዜ ያገኟቸው ቅዳሜ አመሻሽ ላይ እንደሆነ እና አሁን "በሶሪያ ታሪክ ውስጥ አዲስ ዘመን ጀምሯል" ብለዋል። 🟠 የሶሪያ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ተናግረዋል። 🟠 የሶሪያ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ታጣቂዎቹ በደማስቆ ለቀሩት የካቢኔ አባላት ደህንነት ዋስትና እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸውን ይፋ አድርገዋል። 🟠 የእስራኤል ጦር ከሶሪያ ጋር በሚያገናኘው ድንበር የመከላከያ ቀጠና ውስጥ የታጣቂዎች ሰርጎ መግባት ስጋት በመኖሩ "የዜጎችን እና በጎላን ኮረብታ ላይ ያሉ ሰፈራዎችን ደህንነት ለመጠበቅ" ሰራዊቱን እንደሚያሰማራ አረጋግጧል። 🟠 የእስራኤል ጦር በሶሪያ እየተካሄደ ባለው ድርጊት ጣልቃ እንደማይገባ አጽንኦት ሰጥቷል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia