የመጀመሪያው ብሪክስ ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው በአፍሪካ የመጀመሪያው የብሪክስ ፊልም ፌስቲቫል ማስጀመሪያ የሆነው የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል፤ በመጪው ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በሚካሄደው በዚሁ ፌስቲቫል፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ፊልም የሆነው ‘ሂሩት አባቷ ማነው’ እንዲሁም ሌሎች የኢትዮጵያና የቻይና ፊልሞች ለዕይታ እንደሚበቁ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያና ቻይና ፊልሞች በስፋት በሚቀርቡበት በዚሁ መድረክ፤ የብሪክስ ፊልም ፌስቲቫል ይተዋወቃል መባሉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ፌስቲቫሉ የፊልም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ፣ በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን የልማት ትብብር በሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia