" ነፃነት ለቻድ ፈረንሳይ ውጪ!" ቻዳውያን የፈረንሳይ ጦር ሀገራቸውን ለቆ እንዲወጣ ጠየቁፍፁም ሉአላዊነትን እንፈልጋለን ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ቻዳውያን በዛሬው እለት በአብቼ ከተማ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፈኞቹ በቻድ የሚገኙት 1000 የፈረንሳይ ወታደሮች በፍጥነት እንዲወጡ መጠየቃቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተጋሩ ምስሎች አሳይተዋል።ሰልፉ ባለፈው ሀሙስ የቻድ መንግስት ከፓሪስ ጋርወታደራዊ ስምምነት ለማቋረጥ መወሰኑን ተከትሎ የመጣ ነው። ከአብቼ ወደ ኡዳይ የሚወስደው ዋናው መንገድ በሰልፈኞቹ ተይዞ ነበር። አብቼ ብዙዎቹ የቻድ አመፆች የተጀመሩባት ታሪካዊ ከተማ ናት።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia