በሰሜን-ምዕራብ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ስቲልፎንቲን ማዕድን ማውጫ የሰባት ሕገ ወጥ ማዕድን አውጪዎች አስከሬን መገኘቱ ተዘገበ

በሰሜን-ምዕራብ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ስቲልፎንቲን ማዕድን ማውጫ የሰባት ሕገ ወጥ ማዕድን አውጪዎች አስከሬን መገኘቱ ተዘገበየሀገሪቱ የዜና አውታር ኢደበሊውኤን የአካባቢው ሃላፊዎች ጠቅሶ እንደዘገበው ሰዎቹ ከጎርጎሮሳውያኑ ህዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ ከገቡበት ዋሻ ውስጥ መውጣት ሳይችሉ ቀርተዋል ። ዘገባው አክሎ እንደገለጸው ረቡዕ ዕለት 15 ዛማ ዛማዎች (በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከሌሶቶ፣ ሞዛምቢክ እና ዚምባብዌ እና ከመሳሰሉ ጎረቤት ሀገራት የመጡ ሕገወጥ የማዕድን አወጭዎች ስም ነው) ከሃርሞኒ ወርቅ ማዕድን ማውጫ ማርጋሬት ዋሻ መውጫ በኩል ዳግም ወደ ምድር ብቅ ብለዋል።"በቫላ ኡምጎዲ ያለው ስራ በመቀጠሉ በማክሰኞ እና ረቡዕ መካከል መሬት ውስጥ የነበሩ 26 ህገ-ወጥ ማዕድን ቆፋሪዎች በማርጋሬት ዋሻ በኩል መውጣታቸውን" የግዛቱ ፖሊስ ቃል አቀባይ ሲባታ ሞክጋዋቦኔ ለዜና አውታሩ ተናግረዋል።ረቡዕ ዕለት የደቡብ አፍሪካ መንግስት የፕሬስ አገልግሎት እንዳስታወቀው ወደ 150 የሚጠጉ ዛማ ዛማዎች በሳቢ በተተወ የማዕድን ማውጫ ውስጥ መውጣት አልቻሉም። በዘገባው መሰረት ስድስት ሰዎች ከዋሻ በህይወት እንዲወጡ ሲደረግ ሌሎች ሦስት ማዕድን አውጪዎች ህይወታቸው አልፏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik