ሩሲያ በምስራቅ ሜዲትራኒያን ልምምድ ባደረገችበት ወቅት የ "ዚርኮን" እና "ካሊበር" ሚሳኤሎች ተተኮሱልምምዱ የተካሄደው በምስራቅ ሜዲትራኒያን በጎርጎሮሳውያኑ ታህሳስ 1 እስከ 3 ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን የሩሲያ የጦር ኃይል የሥልጠና ዕቅድ አስታውቋል። ይህም ልምምድ በሩሲያ የባህር ኃይል ዋና አዛዥ በአድሚራል አሌክሳንደር ሞይሴዬቭ መሪነት መካሄዱ ተገልጿል። በቪዲዮዎች ላይ እንደታየው ከ "አድሚራል ጎርሽኮቭ" የ"ዚርኮን" ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎችንና ከ "ኖቮሮሲይስክ" ዲዝል-ኤሌክትሪክ ሰርጓጅ ጀልባ የ"ካሊበር" ሚሳኤሎች ሲተኮሱ ታይቷል።በተጨማሪም ከ "ባስቲዮን" የባህር ዳርቻ ሚሳይል ስርዓት የ "ኦኒክስ" ሚሳይሎች የተቶኮሱ ሲሆን በሃይፐርሶኒክ "ኪንዛል" ሚሳይል የታጠቀው MiG-31 ተዋጊ ስራውን ሲያከናውን ታይቷል ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia