ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ከሩሲያ አቻቸዉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በሶሪያ ያለውን ሁኔታ መወያየታቸውን የቱርክ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቀ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው የስልክ ልውውጥ በቱርክ አነሳሽነት የተደረገ መሆኑን ክሪሚሊን በመግለጫው አሳውቋል። በሶርያ እየተባባሰ ስለመጣው ሁኔታ መሪዎቹ ተወያይተዋል።ፕሬዚዳንት ፑትን ፅንፈኛ አሸባሪ ቡድኖች በሶርያ መንግስት ላይ የሚፈፀሙት ወረራ በፍጥነት መቆም አለበት በማለት በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ጨምረውም በሀገሪቱ ሰላም ተመልሶ እንዲሰፍን የሶርያን ህጋዊ ባለስልጣናት ለመደገፍ ጥረት መደረግ አለበት ብለዋል ፤ በተለይም የአንካራን በአካባቢው ያላትን አቅም መጠቀም ይገባል ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia