የራስ ደስታ ዳምጠው የኮከብ ቅርጽ ያለው የወርቅ ሜዳሊያ ለጨረታ መቅረቡን ተከትሎ ቤተሰቦቹ ሜዳልያው እንዲመለስ ጠየቁየኢትዩጲያዊው የጦር ጀግና ቤተሰቦች ከቅደመ አያታቸው ራስ ደስታ የተሰረቀው ሜዳልያ ከጨረታ እንደወጣ ጠየቁ ። ይህ ቅርስ በጎርጎሮሳዊያኑ 1937 የተሰረቀ ባለኮከብ ሜዳልያ ነው።ራስ ደስታ ዳምጠው ሲያዙ በስፍራው ከነበረ የጣልያን ወታደር የተገኘው ሜዳልያው ላይቭ ኦክሽነርስ በተባለ ድህረ ገጽ ላይ ለጨረታ ከቀረቡ ቅርሶች ጋር የተካተተ ሲሆን ከ60,000 እና 90,000 ዩሮ መካከል ግምታዊ ዋጋ ተሰጥቶታል። “ከአያታችን አስክሬን የተወሰደ ሜዳልያ ነው” ሲል የተናገረው በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖረው የራስ ደስታ የልጅ ልጅ የሆነው አማሃ ካሳ፤ በካታሎጉ ላይ ያለውን ጽሑፍ ማንበባችን "ደማችን እንዲፈላ አድርጓል" ብሏል።ሌላኛዋ በአሜሪካ የምትኖረው የራስ ደስታ የልጅ ልጅ ላሊ ካሳ “ በእነዛያ ጊዜያት የተወሰዱ ቅርሶችን መያዝ ሳይታወቅ እንደማይቀር ለአለም ማወቅ አስፈላጊ ነው፤ ከሁሉም የከፋው ደግሞ ታሪካዊ ጠቀሜታቸውን ገንዘብ ለማግኘት መጠቀሙ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው ነው" ስትል ገልጻለች።የራስ ደስታ የልጅ ልጆቹ ሜዳልያው ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዝየም እንደሰሚጥ ተስፋ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።የ አፄ ሃይለስላሴ ተወዳጅ ነበሩ የሚባሉት ራስ ደስታ ዳምጠው በስማቸው በአዲስ አበባ ሆስፒታል ተሰይሞላቸዋል። "ይህ አፀያፊ ያልተገባ በቅኝ ግዛት ወቅት ተሰርቆ የተወሰደ እቃ ላይ ያለ ፍላጎት ነው" በማለት የራስ ደስታን የልጅ ልጆች ወክሎ የተገኘው እና አርት ሪከቨሪ ኢንተርናሽናል የተሰኘ ድርጅት መስራች እና ጠበቃ ክርስቶፈር ማኒርሎ መናገሩን ዘ አርት ጋዜጣ ስለ ቅርሱ በሰራው ዘገባ አመላክቷል።የምእራባውያን ሙዚየሞች በ19ኛው እና 20ኛው ምእተአመታት ከኢትዩጵያ የተሰረቁ ቅርሶችን የያዙ ሲሆን ከመቅደላ የተዘረፈው ጋሻ በታላቋ ብሪታንያ ለሽያጭ ከቀረበበት ጨረታ ተሰርዞ ወደ ሀገርቤት መመለሱ ይታወቃል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia