የሶሪያ ጦር የአሸባሪዎችን ጥቃት በተሳካ ሁኔታ እየመለሰ እንደሆነ እና በቅርቡ የመልሶ ማጥቃት እንደሚጀምር የሶሪያ ጦር ኃይል ዕዝ አስታወቀ

የሶሪያ ጦር የአሸባሪዎችን ጥቃት በተሳካ ሁኔታ እየመለሰ እንደሆነ እና በቅርቡ የመልሶ ማጥቃት እንደሚጀምር የሶሪያ ጦር ኃይል ዕዝ አስታወቀ የሶሪያ ጦር ኃይሎች የሽብር ጥቃቱን በተሳካ ሁኔታ እና በቆራጥነት በመመከት ላይ እንደሆነና፤ በቅርቡ ሁሉንም ግዛቶች ነፃ ለማውጣት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ እንደሚጀምር የሶሪያ ጦር ኃይል ዕዝ በመግለጫው አስታውቋል። "የጦሩ ዕዝ እና የጦር ኃይሎች የሽብር ጥቃቱን የመመከት ሂደት በተሳካ ሁኔታ እና በቆራጥነት እየተካሄደ መሆኑን ያረጋግጣሉ። በቅርቡም ሁሉንም አካባቢዎች ለመቆጣጠር እና ከሽብርተኝነት ነፃ ለማውጣት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ይካሄዳል" ሲል መግለጫው ገልጿል። የሶሪያ ጦር ተጨመሪ ኃይል ሃማ እንደደረሰ እና የመንግሥት ዘመቻ መቀጠሉን የግዛቱ አስተዳዳሪ ካማል ባርሞ ተናግረዋል። የአሸባሪዎች መኪኖች ወደ ሃማ ገብተዋል የሚሉ ዘገባዎች ሀሰተኛ ናቸው ነው ሲሉም አውግዘዋል። የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር የአሸባሪ ቡድኖች በሰሜናዊ ሃማ ግዛት ወደሚገኙ ከተሞች ገብተዋል መባሉን ከእውነት የራቀ ነው ሲል ቀደም ሲል ውድቅ አድርጓል። የሶሪያ ፕሬዝዳንት ባሽር አል-አሳድ፤ ሶሪያ የግዛት አንድነቷን መከልከሏን እንደምትቀጥል እና በአጋር እና ወዳጆቿ ድጋፍ አሸባሪዎችን ድል ማድረግ እንደምትችል ቅዳሜ እለት በድጋሚ ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik