ኬንያ እና ኡጋንዳ የሶማሊያ እና ኢትዮጵያን ግጭት ለመፍታት በጋራ ሊሰሩ እንደሆነ ተገለጸ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ቅዳሜ እለት በታንዛኒያ አሩሻ ተካሄዶ በነበረው 24ኛው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይፋ ያደረጉት ነው። "የሶማሊያ ፀጥታ...ለቀጠናው መረጋጋት እንዲሁም ለባለሀብቶች፣ ነጋዴዎች እና ስራ ፈጣሪዎች እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው" ብለዋል ሩቶ። በኢትዮጵያ እና እራሷን የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ብላ በምትጠራው የሶማሊያ ግዛት መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ፤ አዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ ከጥር ወር አንስቶ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል። ስምምነቱ፤ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ነፃነት ዕውቅና ለመስጠት በሚመስል መልኩ የቀይ ባህር በር መዳረሻ እንድታገኝ የሚያስችለት ነው። ስምምነቱ፤ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የጣሰ እንደሆነ የሶማሊያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia