ናሚቢያ የስፔስኤክስ ስታርሊንክ በሀገሪቱ የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲያቆም አዘዘች የናሚቢያ የኮሙኒኬሽን ቁጥጥር ባለስልጣን፤ ዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን አቅራቢ ያለፈቃድ የሚሰጠውን የሳተላይት ኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎት በአስቸኳይ እንዲያቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል። የናሚቢያ የኮሙኒኬሽን ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሚሊያ ንጊኬምቧ፤ ህዝቡ ሕገ-ወጥ የስታርሊንክ አገልግሎቶችን እንዳይገዛ ወይም እንዳይቀላቀል አስጠንቅቀዋል። ባለሥልጣኑ ሕገ-ወጥ መሳሪያዎችን በመውረስ የወንጀል ምርመራ ከፍቷል። "የናሚቢያ የኮሙኒኬሽን ቁጥጥር ባለስልጣን ፍትሃዊ ውድድርን፣ የሸማቾች ጥበቃን እና የቁጥጥር መስፈርቶችን በማስክበር የኮሚኒኬሽን ህግን ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው። ሁሉም አገልግሎት ሰጪዎች የናሚቢያን የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ በሚመራው የህግ ማዕቀፍ እንዲገዙ እናሳስባለን" ብለዋል። ስታርሊንክ ፈቃድ ለማግኘት ያመለከተ ሲሆን፤ የናሚቢያ የኮሙኒኬሽን ቁጥጥር ባለስልጣን ማመልከቻውን እየገመገመ እንደሆነ ተገልጿል። ባለሥልጣኑ አገልግሎቱን በሚጠቀም ሰው ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል አስጠንቅቆ፤ ህብረተሰቡ ፍቃድ እስኪሰጥ ድረስ ስታርሊንክን ከውጭ ማስገባትም ሆነ መጠቀምን እንዲያቆም አሳስቧል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia